ጤና ጥበቃ ይህ ዓለም አቀፍ ጉባኤ መደረጉ ለአገር ኢኮኖሚ ይጠቅማል ብሎ ከሆነ በሌላ አማርኛ “ሴክስ ቱሪዝም”ን እያስፋፋ ነው
ማለት ነው። ከአገሪቱ ሕዝብ ከግማሽ በላዩ ወጣት እና ሥራ አጥ በሆነባት አገር ገንዘብ ያላቸው ሰዎች ለሴክስ ቱሪዝም እንዲጎርፉባትና
አገሪቱ ካለባት ቅጥ ያጣ ችግር በላይ እንዲህ ዓይነቱ የባህል ወረራ እንዲካሄድባት መንግሥታዊ ማበረታቻ መስጠት ስሕተት ብቻ ሳይሆን
እጅግ በጣም አሳዛኝ ተግባር ነው። በሌላው ዓለም ቢሆን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጋዜጣዊ መግለጫ ለማቋረጥ ከመሔድ ይልቅ ከሕዝብ ሊያገኙት
የሚገባቸውን እምነት ስላጎደሉ ሥልጣናቸውን ወደ መልቀቅ ይሄዱ ነበር።
አገሩ ኢትዮጵያ ስለሆነ አንድ ሚኒስትር የሃይማኖት መሪዎች ያዘጋጁትን ጋዜጣዊ መግለጫ ለማስተጓጎል ቻለ።